የደህንነት ምድብ የድንገተኛ ሁኔታዎች ባለስልጣንን ሁኔታዎቹን ለመቆጣጠር የሚያስፈልጉ ሁሉንም የአሰራር ዘዴዎች የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት። በተጨማሪም የስራ ክፍሉ ለሁሉም መደበኛ የማዘጋጃ ቤት ዝግጅቶች የደህንነት ዝግጅች ኃላፊነት አለበት።

የኃላፊነት መስኮች

እንደ ጦርነት፣ የሚሳኤል ፍንዳታ፣ ርእደ መሬት፣ የውሀ ቀውሶች፣ የአደገኛ ቁሶች ፍንዳታ/ መቀጣጠል፣ የሽብርተኛ ጥቃቶች ያሉ ድንገተኛ ሁኔታዎች ስልጣን ዝግጅት፤

የድንገተኛ ጊዜ የሕዝብ መጠለያዎች ማዘጋጀት፤

ለበጎ ፍቃደኞች የድንገተኛ ጊዜ ሁኔታዎች ስልጠና መስጠት፤

የማዘጋጃ ቤት ዝግጅቶች የደህንነት ጥበቃ ማድረግ፤

ከመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የሀገር ውስጥ የፊት ትእዛዝ መስጫ ጋር በመተባበር የድንገተኛ ጊዜያት የደህንነት አሰላለፍን ማሻሻል።