የማስጠንቀቂያ ቀጠና: ወይም ይሁዳ

የመከላከያ ቀጠና፡ ዳን

ወደ ደህንነት ዞን ለመድረስ የተመደበ ጊዜ - አንድ ደቂቃ ከሰላሳ ሰከንዶች።

አንድ ሰው ወደ ደህንነት ዞን መግባት እና 10 ደቂቃዎች ያህል ውስጥ መቆየት አለበት።

አንድ ሰው የደውል መጥሪያ ድምጽ ከሰማ በኋላ በተመደበው የቆይታ ጊዜ ውስጥ ወደ ደህንነት ዞን መግባት አለበት።

የደህንነት ዞን መምረጥ

የደህንነት ዞን ከዚህ በታች በተመለከቱት አማራጮች ላይ ተመስርቶ የደውል ድምጽ ከተሰማ በኋላ ባለው የተመደበ የቆይታ ጊዜ መሰረት ይመረጣል፡-

 1. ማማድ (የደህንነት ዞን በአፓርታማ) ወይም ማማክ (የደህንነት ዞን በወለል/ፎቅ)

 2. ከቦምብ መጠለያ

ሀ. ከቦምብ መጠለያ ከውስጥ የሚሰራና በህንጻ ውስጥ የሚገኝ እና በማስጠንቀቂያ ጊዜ ለብቻ በተሰራ የየደረጃ መወጣጫ መድረስ የሚቻል የአፓርታማ ህንጻ ነው።

ለ. የህዝብ ከቦምብ መጠለያ - የደውል መጥሪያ ድምጽ ከጠራ በኋላ በተመደበው የቆይታ ጊዜ ውስጥ መድረስን የሚጠይቅ ነው።

 1. የውስጥ የደረጃ መወጣጫ

ሀ. የደህንነት ዞን በአፓርታማ ወይም በፎቅ/ ወለል፣ የውስጥ መጠለያ ሳይኖራቸው የተሰሩ ከሶስት በላይ ፎቅ ያላቸው ህንጻዎች የላይኛው አፓርታማዎች ነዋሪዎች ሁለት ወለሎች ወደ ታች በመውረድ ደረጃ መወጣጫዎቹ ላይ ይቆያሉ። ከሶስት በላይ ፎቆች ባሉት ህንጻ ውስጥ ሁሉም የደረጃ መወጣጫዎች ከምድር ቤት ወለልና የላይኞቹ ሁለት ፎቆች በስተቀር ዝግ ይሆናሉ።

ለ. የደህንነት ዞን በአፓርታማ ወይም በፎቅ/ ወለል፣ የውስጥ መጠለያ ሳይኖራቸው የተሰሩ ባለ ሶስት ፎቅ ያላቸው ህንጻዎች የላይኛው አፓርታማዎች ነዋሪዎች አንድ ወለሎች ወደ ታች በመውረድ ደረጃ መወጣጫዎቹ ላይ ይቆያሉ። በባለ ሶስት ፎቅ ህንጻዎች ውስጥ እጅግ ጥበቃ የሚደረግላቸው (ዝግ) የደረጃ መወጣጫዎች የሁለተኛው/ መካከለኛው ፎቅ የደረጃ መወጣጫ ነው።

 1. ምንም የደህንነት ዞን በአፓርታማ ወይም ፎቅ፣ ወይም የውስጥ መጠለያ፣ ወይም የደረጃ መወጣጫ በማይኖርበት ሁኔታ አንድ ሰው አነስተኛ ውጫዊ ግድግዳዎች፣ መስኮቶችና መውጫዎች ያሉት የውስጥ ክፍል መምረጥ አለበት።

 

ያስታውሱ

 • በድንገተኛ ጊዜ ውጭ የሚገኙ ሰዎች እንዲጠቀሙበት ለማስቻል የመግቢያ በሩን ክፍት አድርገው ይተዉ፤
 • በባኞ ቤት ወይም ሻወር ቤት ለመቆየት መምረጥ የለብዎትም። ከሴራሚክ ወይም ሌሎች ጡቦች እና ሊጋርድ/ ሊዘጋ ከሚችል መስታወት ይራቁ፤
 • በህንጻ አቅራቢያ የሚሳኤል መፈንዳትን ተከትሎ በፍንጣሪዎችና የፍንዳታ ሞገዶች ምክንያት ሊደርስ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል ሲቪል ዜጎች በህንጻዎች የመግቢያ በሮች ላይ መቆየት የለባቸውም።

 

በደህንነት ዞን ውስጥ ለተራዘመ ቆይታ የሚመከሩ መሳሪያዎች

 • በየወቅቱ መረጃ መለዋወጥ የሚቻልበት መገናኛ (ኮምፒውተር፣ ቲቪ፣ በባትሪ የሚሰራ ራዲዮ)
 • ተቀያሪ ባትሪዎችና ቻርጀር ያለው የሞባይል ስልክ
 • ለእያንዳንዱ ሰው በቀን ሶስት ሊትር የተሸገ የጠርሙስ ውሀ። ለ3 ቀናት የሚያገለግል ውሀ ማዘጋጀት ይመከራል
 • እንደ ጣሳዎችና ካርቶኖች ባሉት ማሸጊያዎች የታሸጉ ምግቦች
 • የድንገተኛ ጊዜ መብራት (ኤልኢዲ)፣ ፍላሽላይትና ባትሪዎች
 • የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ ኪት፣ መድሀኒቶች
 • የእሳት ማጥፊያ
 • የአስፈላጊ ሰነዶች፣ የህክምና ሰነዶች፣ ለመደበኛ የመድሀኒት አወሳሰድ የመድሀኒት ማዘዣዎች፣ መታወቂያ፣ የግል ሰነዶችና የገንዘብ ሰነዶች ኮፒዎች
 • በቅጽበት ለቆ መውጣት የሚስፈልግ ከሆነ ለጥቂት ቀናት የሚያገለግሉ የግል እቃዎችን በሻንጣ፤
 • የድንገተኛ ጊዜ ድርጅቶች፣ ዘመዶችና ጎረቤቶች ስልክ ቁጥሮች ዝርዝር፤
 • ነገሮችን የሚያቀሉ እንደ ጌሞች፣ መጽሄቶች፣ መጻህፍት ያሉ ቁሳቁሶች
 • ችግሮችና ፍላጎቶችን መሰረት አድርጎ ለቤተሰብዎ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ እቃዎች