የመጽሀፍ ቅዱስ ማመሳከሪያነት

የኡኖ መሬት በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ በመጽሀፈ ነሕሚያ (6፡2) ላይ ተገልጿል። አፈ ታሪክ እንደሚነግረን በጆሽዋ ዘመን ቦታው ዙሪያው በግድግዳ የታጠረ ነበር። ከክርስቶስ ልደት በፊት በ445 አመተ አለም የቤንጃሚን ትውልድ በክልሉ ለም አካባቢ ለመስፈር ሲል ወደ ቦታው መጣ። ኦኖ በሚናስ ውስጥ የተገለጸችና በዚህ አገላለጽ እና የኦር የሁዳ ከተማ አካል በሆነው በአና መንደር መካከል ግንኙነት ያለ ሲሆን በዚህ ቦታ ላይ ሰፈራ የተጀመረው ከጥንት ዘመን ጀምሮ መሆኑን የሚያረጋግጡ የከርሰ ምድር ጥናት ግኝቶች ተገኝተዋል።

በነጻነቱ ጦርነት ወቅት የቺሪያ፣ ስኪያ እና ክፋር አና የተባሉት የአረብ መንደሮች በ‹‹ቻማቴዝ›› ዘመቻ ወቅት በአሌክሴንድሮኒ ጦር ተይዘዋል። በዚህ መንደር ነዋሪዎች ጥለዋቸው የሄዱ መኖሪያ ቤቶችን በ1949 ዓ.ም የኦር ይሁዳ የመጀመሪያ ሰፋሪዎች ተጠቅመውባቸዋል።

የከተማዋ ስም

ከተማዋ ስያሜዋ የተሰጣት በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ የዩጎዝላቪያ ነዋሪና በአውሮፓ ውስጥ ከሀይማኖታዊ - የተግባር ፖለቲካ ጽዮናዊነት አራማጆች አንዱ ከነበረው ራቢ የሁዳ ሽሎሞ ቻይ አልኬላይ ስም በመነሳት ነው። ሌሎች ደግሞ የስሙን ስያሜ በቱርክ፣ ኢዝሚር ከሚገኘው ከቱርክ የሚመጡ ስደተኞች የእስራኤላውያንን ህብረትን ከመቀላቀላቸው በፊት ስልጠና ይወስዱበት ከነበረው ‹‹የይሁዳ እርሻ ቦታ›› ጋር ያገናኙታል።

የመጀመሪያዎቹ ስደተኞች

የነጻነቱን ጦርነት ተከትሎ አዳዲስ ስደተኞች ወደ ኦር ይሁዳ የመጡ ሲሆን በመቀጠልም አንዱ ሌላውን ማምጣት ጀመረ። የመጀመሪያዎቹ ሰፋሪዎች የደረሱት በ1949 ዓ.ም ነበር። እነዚህ ሰፋሪዎች በራሳቸው ፍቃድ በሀፊያ የሚገኘውን ሻር አሊያ መጠለያ ካምፕን ለቀው የመጡ የቱርክ ስደተኞች ነበሩ። በተመሳሳይ አመት ከሊቢያ የመጡ ስደተኞች በከተማዋ ሰፍረዋል። ሰፋሪዎቹ ተለቀው በሄዱ የስኪያና ክፋር አና የአረብ መንደሮች እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በጭቃ ቤቶች ይኖሩ የነበረ ከመሆኑም በተጨማሪ ውሀ የሚያገኙት ከቴል ሊትዊኒስኪ (አሁን ቴል ሀሾመር ተብሎ ከሚጠራው) ርቀት ሄደው በባልዲ በመቅዳት ነበር። በ1950 ዓ.ም የመጀመሪያው የማረፊያ ካምፕ– ማባራ- በስኪያ ኤ የተቋቋመ ሲሆን ከ1950-1953 ስደተኞች ‹‹በእዝራና ነህሚያ›› ዘመቻወች ከኢራቅ ወደ ካምፑ የደረሱ ሲሆን በአብዛኞቹ ሁኔታዎች ስደተኞቹ የቦታው ሰፋሪ ነዋሪዎች አባላት ተደርገው ነበር። የስኪያ ኤ እና ቢ፣ እና የክፋር አና ኤ እና ቢ የመጠለያ ካምፖች በመቀጠል የተቋቋሙ ሲሆን ስደተኞች በድንኳኖች እና ከዝናብ ወቅት በኋላ እንደ ጅብ ጥላ ይፈራርሱ በነበሩ ጎጆዎች ውስጥ ነበር። እያንዳንዱ የመጠለያ ካምፕ የራሱ የአስተዳደር ኮሚቴ ነበረው። በአስቸጋሪው የ1951/2 የክረምት ወቅት ህጻናት በቴል ሀሾመር ወደሚገኘው የወታደራዊ ካምፕ እና ቀጥሎም ወደ ግለሰብ መኖሪያ ቤቶችና ኪቡትዚም ይላኩ ነበር።

የከተማዋ የስራ እድል ሁኔታ

በከተማዋ የነበረው ስራ የማግኘት ሁኔታ አስቸጋሪ ነበር። የከተማዋ ነዋሪዎች ስራ ይሰሩ የነበረው በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በደቦ የሚሰሩ የጉልበት ስራዎችን የነበረ ሲሆን ይህም ለአመጾች መነሳት መንስኤ ይሆን ነበር። በ1952 ዓ.ም የነበሩትን ሁኔታዎች ለማሻሻል አላማ ከሁሉም የመጠለያ ካምፖች የተውጣጡ አባላትን የያዘው የጋራ ኮሚቴ– ሀቫድ ሀሜቻድ– የተቋቋመ ቢሆንም ኮሚቴው የገንዘብ ችግሮች አጋጥመውት ነበር። ከነዋሪዎች የአካባቢው ባለስልጣን እንዲቋቋም በመጠየቅ ለሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር የቀረቡት ማመልከቻዎች የሰፈራ ቦታው ለጊዜያዊ መኖሪያ ቦታነት ብቻ ታስቦ የተዘጋጀ የነበረ በመሆኑ ምክንያት ማመልከቻዎቹ ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተዋል። ምንም እንኳን ከድንኳን ወደ ጎጆ ቤቶች ሽግግር ይደረግ የነበረ ቢሆንም የነበሩት አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደነበሩ ቀጥለው የነበረ ከመሆኑም በተጨማሪ የተማሩና ለአስተዳደሩ የተሻለ ቅርበት የነበራው ነዋሪዎች የሰፈራ መንደሮቹን ለቀው ወደ ቴል አቪቭ እና ራማት ጋን ይሄዱ ነበር።

የኦር የሁዳ ቋሚ መኖሪያ ቦታ መሆን

በ1955 ዓ.ም የኦር የሁዳ ቋሚ የመኖሪያ ቦታ መሆን የታወጀና በ1962 ዓ.ም የከተማዋ ካውንስል የተመረጠ ሲሆን ለከተማዋ የመዘጋጃ ቤት እቅድ እንዲዘጋጅ ሀሳብ ቀርቧል። በስልሳዎቹ የከተማዋ ነዋሪዎች የአኗኗር ሁኔታዎችና የስራ እድሎች እየተሻሻሉ ከመምጣታቸውም በተጨማሪ አብዛኞቹ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች መንግስት/ አስተዳደር ማቋቋም ወደጀመሩ ሌሎች ቦታዎች ለቀው መሄድ ጀመሩ (በ1958 ዓ.ም)። የግንባታው መጠን በፍጥነት እየጨመረ ከመሄዱም በተጨማሪ መኖሪያ መንደሩ በክልሉ ከሚገኙ ከተሞች ጋር በመንገድ መገናኘት ቻለ።

ኦር የሁዳ ከተማና የእራኤል እናትነት

በአስራ ዘጠኝ ሰባዎቹና ዘጠናዎቹ ኦር የሁዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ከጆርጂያ፣ ቡካራ እና የቀድሞው ዩኤስኤስአር የመጡ ስደተኞችን ተቀብላለች። በአስራ ዘጠኝ ሰማኒያዎቹ አጎራባች ቦታዎችን በማደስ ፕሮጀክት መዋቅር ስር ኦር የሁዳ ከሚልዋኪ፣ ዩኤስኤ እና ኦንታርዮ ካናዳ በመጡ አይሁዳውያን ማህበረሰቦች ተወሰደች። እንደ ፕሮጀክቱ አንድ ክፍል የአካባቢው ካውንስል በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በአሚዳር (የእስራኤል መቋቋምን ተከትሎ የመኖሪያ ቤቶችን ይገነባ የነበረ የመንግስት የግንባታ ኩባንያ) ይኖሩባቸው የነበሩ አፓርታማ ቤቶችን መግዛት የሚችሉበት መርሀግብር የነደፈ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ካውንስሉ በቤቶች ሚኒስቴር ይካሄዱ የነበሩ የአዳዲስ የአፓርታማ ግንታዎችን በመተው በሺዎች የሚቆጠሩ አፓርታማዎች በካውንስሉ እቅድ ታግዘው በነዋሪዎቻቸው እንዲስፋፉ አቋም በመያዙ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ያረጁ አፓርታማዎች ለአዲስ ተጋቢ ወጣት ጥንዶች ተሻሽለው ተገነቡ። በ1988 ዓ.ም ኦር ይሁዳ ከተማነቷና የእስራኤል እናትነቷ በይፋ ታወጀ።

የአዳዲስ አጎራባች መንደሮች ግንባታ

በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ኦር የሁዳ በአጎራባች ኒቭ ሳቭዮን አዲስ አጎራባች መንደር ለመገንባት ‹‹ከአፍሪካ እስራኤል›› ጋር ውል የተፈራረመች ሲሆን ይህም በተለያዩ ልዩነቶች የሚገነቡ 2500 መኖሪያ ቤቶች ግንባታን የሚይዝ ነበር። በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ የህዝብ ተቋማት የተገነቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ጥቂቶቹ የባህል አዳራሽ፣ ቤተ መጻህፍት፣ የሳይንስና ሥነ ጥበብ/ አርት ማዕከል፣ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የእግር ኳስና የቴኒስ ሜዳዎች እና አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ይገኙበታል።

ከጥቂት አመታት በኋላ የአዲስ መኖሪያ መንደር ግንባታ እቅድ የተዘጋጀና የግንባታ ስራው በፍጥነት የተጀመረ ሲሆን ይህም በከተማዋ ምስራቅ ክፍል የሚገኘው የኒቭ ራቢን የመኖሪያ መንደር ነበር። በተጨማሪም አዳዲስ የንግድና የስራ ፈጠራ ማዕከላት የማልማት ስራ የተጀመረ ሲሆን በከተማዋ ደቡባዊ ክፍል በሚገኘው ሀሎም የኢንዱስትሪ መንደር ተገነባ። በ2000 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በኦር የሁዳ የትምህርት ተቋማት ግንባታ የተጀመረ ሲሆን ለምሳሌ ያህልም የሄክ የትምህርትና ጥናት ማዕከል እና ቅርንጫፉ የኦኖ የትምህርት ኮሌጅ ይጠቀሳሉ።

በ2007 ዓ.ም በገንዘብ ችግር የተነሳ የኤፋል አካባቢያዊ ካውንስል መፍረስን ተከትሎ ራማት ፒንቻስ ከኦር ይሁዳ ጋር በመቀላቀል ከከተማዋ የመኖሪያ መንደሮች መካከል አንዷ ሆነች።

ዛሬ ላይ: በትምህርትና የመሰረተ ልማት ማሻሻያ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት

ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ የኦር የሁዳ ማዘጋጃ ቤት ለእድገት ቁልፍ እንደሆነ አድርጎ በሚመለከተው ትምህርት ላይ ትኩረቱን በማድረግ በበርካታ የተለያዩ የአኗኗር ዘርፎች ላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ላይ ነው። ‹‹የመኖሪያ ቤት ስምምነት›› መፈረምን ተከትሎ በከተማዋ የሚኙት ሁሉም የትምህርት ተቋማት፣ የህዝብ የአትክልት ቦታዎችና ፓርኮች፣ ለአስርት አመታት ተዘንገተው የነበሩ የፍሳሽ ማስተላለፊያ መሰረተ ልማቶች እና መንገዶች የደረጃ ማሻሻያ ይደረግላቸዋል። ባረጁ የመኖሪያ መንደሮች ላይ ከሚደረገው ኢንቨስትመንት ጎን ለጎን በከተማ ሁለት አዳዲዲስ የመኖሪያ መንደሮች ግንባታ የተዋወቀ ሲሆን እነዚህም ከመንገድ 461 በስተሰሜን የሚገነባው ቤይት ባ ፓርክ እና የናቻል አያሎን ማስፋፊያ አንድ ክፍል የሆነው ፓርክ አያሎን ናቸው።

ከዚህ በተጨማም ማዘጋጃ ቤቱ የማፍረስና መልሶ ግንባታ መርሀግብሮቹን የሚያስፈጽምለት የማዘጋጃ ቤት የኢኖቬሽን የስራ ክፍልን እና ያረጁ መኖሪያ መንደሮችን ደረጃ ለማሻሻል እና ለነዋሪዎች ደረጃው ከፍ ያለ የአኗኗር ሁኔታ ለመፍጠር ታማ 38ን አቋቁሟል።