ስማርት ከተማ

ስማርት ከተማ ለነዋሪዎቹ በሚያቀርበው ከፍተኛ ደረጃ አገልግሎት ረገድ እጅግ አስተማማኝ ከመሆኑም በተጨማሪ የከተማውን ሀብቶች በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም ለነዋሪዎቿና ለከተማዋ የወደፊት ሁኔታ አመቺ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የከተማዋን አሁን ያለውን ዳታ ይጠቀማል። ስማርት ከተማ ለችግሮች መፍትሄዎችን አስቦ ከማቅረብ በተጨማሪ የተለያዩ የድንገተኛ ጊዜ ሁኔታዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ የመቋቋም አቅም አለው። ስማርት ከተማ ካሉት አጠቃላይ ችሎታዎች መካከል ለነዋሪዎች የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ለማሻሻል እንደ በከተማዋ ባጠቃላይ ነጻ የኢንተርኔትን ተደራሽ ማድረግ፣ አገልግሎቶችን በኢንተርኔት አማካኝነት ተደራሽ ማድረግ፣ የነዋሪዎችን ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ለመቀበል የግንኙነት ማዕከላት እንዲኖሩ ማድረግ፣ በተለያዩ የማዘጋጃ ቤት የስራ ክፍሎች መካከል ያሉ የውስጥ ግንኙነት ዘዴዎችን ማሻሻል፣ ወዘተ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማል።

ከአካባቢ ጉዳዮች አንጻር ለነዋሪዎች ከፍተኛ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶች ማቅረብ ላይ አጽዖት በመስጠት ስማርት ከተማ ያሉ ሀብቶችን በተቻለ መጠን በተሻለ መልኩ ለመጠቀም፣ የአካባቢ ጥራትና የነዋሪዎችን ጤና ለመጠበቅ ይተጋል። በአብዛኛው ሁሉም እነዚህ ስራዎች በገንዘብ፣ ማህበራዊና የአካባቢ ወጪዎች መካከል ምጣኔን በመፍጠር ይከናወናሉ።

ኦር ይሁዳ – ስማርት ከተማ

የኦር ይሁዳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ከፍተኛ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶች ከጥሩ ተደራሽነትና ውጤማነት ጋር የምታቀርብ ስማርት ከተማ የማድረግ ግብ አስቀምጧል። በ2017 ዓ.ም አጠቃላይ ጥናት ካካሄደና የከተማዋን ፍኖተ ካርታ ካዘጋጀ በኋላ ማዘጋጃ ቤቱ ዋና ትኩረቱን ቴክኖሎጂ እና ለስማርት ከተማ ቀጥለው የሚሰሩ ተጨማሪ ሲስተሞች ለነዋሪዎች የተሻሉ አገልግሎቶች ማቅረብን መሰረት የሚያደርጉበት ጠንካራና እጅግ ዘመናዊ መሰረተ ልማት መዘርጋት አድርጎ ስራውን ማካሄድ ጀምሯል።

በማዘጋጃ ቤት የስራ ጣቢያዎች መካከል ያለ የኢንተርኔት ግንኙነት

የኦፕቲክ ፋይበር ዝርጋታን እንደ አመቺ የመገናኛ ዘዴ አድጎ ከሚመለከተው መደበኛ የአሰራር ስርአት በተለየ ኦር ይሁዳ ሚሊሜትር የሞገድ ቴክኖሎጂ (EHF) ተብሎ የሚጠራ የተለየ፣ የፈጠራና አዲስ ግኝት የሆነ አቀራረብ መከተልን መርጣለች። ይህ ገመድ አልባ የስርጭት ዘዴ ሲሆን አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ተቀባይነት ያገኘውን የዋይፋይ/ WIFI ሲስተም የስርጭት ፍጥነት በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል። እያንዳንዱ እነዚህ ገመድ አልባ ማሰራጫ መስመሮች ከዳታ ስርጭት ፍጥነትና በሁለት ነጥቦች መካከል በተዘረጋው የኦፕቲክ ፋይበር መስመር ዳታ ከማስተላለፍ አስተማማኝነት አንጻር አንድ አይነት ናቸው። በዘመናዊ ድሮን አማካኝነት በቦታዎች ላይ የተካሄደው የዳሰሳ ጥናት ሁሉንም የማዘጋጃ ቤት የስራ ጣቢያዎች ከማዘጋጃ ቤት ዋና መስሪያ ቤቶችና የድንገተኛ ጊዜ ክፍል ጋር በገመድ አልባ ማሰራጫ መስመሮች አማካኝነት ለማገናኘት የሚያስችል ትክክለኛ የቦታ ካርታ አስገኝቷል። የሚሊሜትር ሞገድ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የማዘጋጃ ቤት የግንኙነት ሲስተም ማዘጋጀት ማዘጋጃ ቤቱን ለገመድ አልባ መገናኛና የስልክ አቅራቢዎች የሚያወጣውን ወጪ በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ያስችለዋል። ቴክኖሎጂው ማዘጋጃ ቤቱን በውጭ አቅራቢዎች ላይ ጥገኛ ሳይሆን የተቀናጁ የግንኙነት ሲስተሞችን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር ያስችለዋል። ቴክኖሎጂው በተጨማሪም ለሁሉም የማዘጋጃ ቤት የስራ ክፍሎች ዳታ በቀጥታና ወዲያውኑ ለማስተላለፍ ያስችላል። የቴክኖሎጂው ዝርጋታ ስራ ሲጠናቀቅ በከተማዋ በጠቅላላው የሚገኙ የህዝብ ህንጻዎች፣ ፓርኮችና የህዝብ አረንጓዴ ቦታዎች ነጻ የዋይፋይ ኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛሉ።

የደህንነት ቅኝት ካሜራ ኔትወርክ

የደህንነት ቅኝት መቆጣጠሪያ ካሜራዎች ከተማዋን በስፋት የሚያዳርሱ ከመሆኑም በተጨማሪ በሪል ታይም ለማዘጋጃ ቤት ዋና መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ዳታ ያስተላልፋሉ። ስለሆነም ከተማዋ ለነዋሪዎቿ የበለጠ አስተማማኝ የደህንነት ሁኔታ መፍጠር እና በከተማዋ በየትኛውም ቦታ ለሚያጋጥም የትኛውም ክስተት ፈጣን ምላሽ መስጠት ትችላለች። ይህ ዘመናዊ የኢንተርኔት ቅኝት ኔትወርክ ለከተማዋ ቀላልና ፈጣን ሌይአውት በአነስተኛ ወጪ እንዲኖራት ያስችላታል።

ስማርት የመንገድ መብራት

ስማርት የመንገድ መብራት ሀይል ቆጣቢና በከፍተኛ ደረጃ ቆጣቢ ከመሆኑ በተጨማሪ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም የመንገድ መብራቶች በመቆጣጠሪያ ሲስተም አማካኝነት በቀጥታ ለመቆጣጠር ያስችላል። ሲስተሙ በሚፈለጉት መስርቶች ላይ ተመስርቶ መብራቶችን የማብራትና የማጥፋት ብሎም የማደብዘዝ ውሳኔ ለመወሰን ያስችላል። ይህ አጠቃላይ መቆጣጠሪያ በአላስፈላጊ ሰአቶች እንደ የህዝብ ፓርኮችና የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ባሉ ቦታዎች የሚካሄዱ አላስፈላጊ መሰባሰቦችን መብራቶቹን በተወሰነ ጊዜ በማደብዘዝ ወይም በማጥፋት እና በማጉላት ወይም በማብራት ለመከላከል ያስችላል። ሲስተሙ እንደ አስፈላጊነቱ በአደጋ ወይም ረብሽ ወቅት ለተወሰነ ቦታ ብርሀን እንዲያገኝ ለማድረግ ያስችላል።

ክላውድ የስልክ ስዊች ቦርድ

ይህ አዲስ የስልክ ሲስተም ከአጸደ ህጻናትና የቀን እንክብካቤ ማዕከላት አንስቶ እስከ ትምህርት ቤቶች፣ የማዘጋጃ ቤት የስራ መምሪያዎችና ዋና መስሪያ ቤት ድረስ የሁሉንም የማዘጋጃ ቤት የስራ ክፍሎች ሁሉንም የዳታ ስራ ያቀናጃል። አዲሱ የተቀናጀ ኔትወርክ ከፍተኛ ደረጃ አገልግሎት ማቅረብ በማስቻል የመገናኛ ወጪዎችን ይቀንሳል በተለይም ከማዘጋጃ ቤት ዋና መስሪያ ቤቶች በርቀት ለሚገኙ የስራ ክፍሎችና ጣቢያዎች። በፕሮጀክቶቹ የመጀመሪያ ዙር ላይ የደረጃ ማሻሻያ ከሚደረግባቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱ የማዘጋጃ ቤት የስልክ የውስጥ ሲስተም ነው። ለሁሉም የማዘጋጃ ቤት ክፍሎች የተለያዩ አማራጮችና የመስራት አቅሞች ያሏው እጅግ ዘመናዊ የስልክ መስመሮች ይገጠሙላቸዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁሉም የስራ መምሪያዎች አንድ አይነት የሲስተም ማውጫ ይኖራቸዋል። ይህ የውስጥ አገልግሎቶችን እና የማዘጋጃ ቤት የብቃት ደረጃዎችን ለማሻሻል አንዱ ቀላል ደረጃ ሲሆን በውጤቱም ለነዋሪዎች የሚቀርቡ አገልግሎቶች ደረጃዎችን ማሳደግ ያስችላል።