‹የመኖሪያ ቤት ስምምነት› ማለት የአፓርታማ መኖሪያ ቤቶች አቅርቦትን በፍጥነት ለማሳደግ በእስራኤል መንስት፣ የእስራኤል የመሬት አስተዳደር (አይኤልኤ) የፋይናንስ ሚኒስቴር፣ የቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የአካባቢ ባለስልጣናት መካከል የሚፈጸም ስምምነት ነው። ስምምነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን የያዙ የመኖሪያ መንደሮች በስምምነቱ ፈራሚ የአካባቢ አስተዳደሮች ውስጥ ለመገንባት ያስችላል።

በዚህ ስምምነት መዋቅር ስር መንግስት ለአካባቢው አስተዳደር ለህዝብ መኖሪያ ቤቶች ህንጻዎች፣ የትምህርት ቤት ተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታ የመጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት ግዴታ የሚገባ ሲሆን ይህ የሚደረገው ፕሮጀክቱ ለገበያ ትውውቅ ከመቅረቡ በፊት ነው። የአካባቢው ባለስልጣን/ አስተዳደር ለኢንተርፕሪነሮች በ90 ቀናት ውስጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት ግዴታ ይገባል። በዚህ ስምምነት መዋቅር ስር የፕሮጀክቱን አካሄድ ለማፋጠን ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ ይዘጋጃል።

የመኖሪያ ቤት ስምምነት – ኦር ይሁዳ

ኦር ይሁዳ ወይም ‹የመኖሪያ ቤት ስምምነት› በ04/04/2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤኒያሚን ኔታንያሁ፣ የግምጃ ቤት ሚኒስትሩ ሞሼ ካችሎን፣ የቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ ዮአቭ ጋላንት፣ የእስራኤል የመሬት አስተዳደር ዳይሬክተሩ አዴል ሺምሮን እና የኦር ይሁዳ ከንቲባ ሊያት ሾቻት በተገኙበት ተፈርሟል።

በተፈረመው ስምምነት መዋቅር ስር የእስራኤል የመሬት አስተዳደር በከተማዋ 5020 አዳዲስ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን ለገበያ ያቀርባል። እቅዱ በቀጣዩ አመት ለመጀመር እንደታሰበው 1870 አዳዲስ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን እንደሚይዘው ‹‹ፓርክ አያሎን›› የመኖሪያ መንደር ያሉ አዳዲስ የመኖሪያ መንደሮች ልማትን ያጠቃልላል። የመኖሪያ ቤት ስምምነት እቅዶቹ ቀጣይ ግንባታዎች እ.ኤ.አ 2018-2020 ለገበያ የሚቀርቡ ሲሆን እነዚህም 2350 አዳዲስ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን በአጎራባች በ64 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ለመፍጠር ከታቀዱት የስራ እድሎች ጋር የሚይዘውን የ‹‹ፓርድሬስ በቺሳቾን›› የመኖሪያ መንደርን፣ እና በአጎራባች የሚገኘው 1870 አዳዲስ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን በ800 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ለመፍጠር ከታቀዱት የስራ እድሎች ጋር የሚይዘውን የ‹‹ፒንካስ ኦን ዘ ፓርክ›› መኖሪያ መንደርን ያጠቃልላሉ።

ከአዳዲስ የመኖሪያ መንደሮቹ በተጨማሪ ስምምነቱ በደቡባዊ አካባቢ በ20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ለስራ ፈጠራ የሚደረግ ግንባታ የስራ እድል ልማትን የሚይዝ ሲሆ በከተማዋ ዙሪያ ጎርፍን ለመከላከል የፍሳሽ ማስተላለፊያ ሲስተም ይገነባል። የኦር ይሁዳ ‹የመኖሪያ ቤት ስምምነት› መሪ እና እጅግ ወሳኙ ክፍል በአከታማዋ የረጅም ዘመን አጎራቾች፣ የህዝብ ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ መንገዶች የፍሳሽ ማስተላለፊያ መሰረተ ልማቶች፣ ለአዲስ ፓርኮች ግንባታና ነባር ፓርኮች ደረጃ ማሻሻያ፣ እና በከተማዋ ባጠቃላይ የብስክሌት መንገዶች ለመገንባት የሚካሄደው ኢንቨስትመንት ነው።

‹የመኖሪያ ቤት ስምምነቱ› መሪ መርህ ለመሰረተ ልማቶች፣ የህዝብ ህንጻዎች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የትራንስፖርት ማቋረጫዎች፣ ፓርኮች፣ እና የንግድና የስራ ፈጠራ ቦታዎች በመንግስት የሚሰጠው የመጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ ነው። ‹የመኖሪያ ቤት ስምምነቱ› ለኢንተርፕሪነሮች በ90 ቀናት ውስጥ አስፈላጊ ፍቃዶችን እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን ይህም የአዳዲስ የመኖሪያ መንደሮቹን የግንባታና ልማት የጊዜ ሰሌዳ ያሳጥራል። ከዚህ በተጨማሪም ‹የመኖሪያ ቤት ስምምነቱ› የእያንዳንዱን የፕሮጀክት ደረጃ የአፈጻጸምና አካሄድ የጊዜ ሰሌዳዎች በግልጽ ያስቀምጣል።

ከስምምነቱ መፈረም በኋላ ባለስልጣኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን ለማልማትና ለመገንባት ከመንግስት የአሰራር ዘዴዎችና ድጋፍ ያገኛል። ‹የመኖሪያ ቤት ስምምነቱ› በሀገሪቱ ማእከላዊ ክልል እያደገ ለመጣው አዲስ ተጋቢ ወጣት ጥንዶች የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ተያያዥ ምላሽ ለመስጠት በሞዴልነት ታስቦ የተዘጋጀ ስምምነት ነው። እነዚሀ ስምምነቶች ላሉት፣ ትኩረት የሚደረግባቸው ቦታዎችና ውጤታማ የገበያ አቅርቦት በቅድሚያ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትን የሚቀጥሩ ሲሆን ይህም ከስምምነቱ ፈራሚ የአካባቢው አስተዳደር ጋር በመተባበር ይፈጸማል።

የ‹የመኖሪያ ቤት ስምምነት› ባለስልጣንን ለማግኘት – እዚህ ጋር ይጫኑ