ስለ ከተማዋ

ኦር ይሁዳ-ራማት ፒንካስ በእስራኤል ውስጥ በመካከለኛ ዳን ክልል የምትገኝ እና የቢካት ኡኖ (የኡኖ ሸለቆ) አካል የሆነች ከተማ ነች። ከተማዋ ከቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያ 7 ኪሎሜትር የምትርቅ ሲሆን፣ ይሁድ ሞኖሶን (በምስራቅ አቅጣጫ)፣ ሩት 461 እና ቴል ሃሾመር (በሰሜን አቅጣጫ)፣ ሩት 412 (በደቡብ አቅጣጫ) እንዲሁም ጌሃ (በመዕራብ አቅጣጫ) ያዋስኗታል። የከተማዋ የቆዳ ስፋት 6500 ኤከር ገደማ ነው።

ኦር ይሁዳ እ.አ.አ. በ1949 የተመሰረተች ሲሆን፣ መጠሪያዋንም ያገኘችው ከቀደምት ከጽዮናዊያን ውስጥ አንዱ ከሆነው እና ስለ ዕብራይስጥ ቋንቋ ተሃድሶ ከተናገረው ከራቢ ይሁዳ ቤን ሽሎሞ ቻይ አልካላይ ስም ነው። ከተማዋ በማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ምጣኔ ደረጃ ከ10 6ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን በአሁኑ ወቅት በግምት 37,000 ነዋሪዎች እዚህ ይኖራሉ።

የከተማዋ ራዕይ

ኦር ይሁዳ-ራማት ፒንካስ መላውን የኦኖ ሸለቆ ክልልን የሚያገናኝ ሲሆን የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችን ለሁሉም አዋሳኝ አስተዳደሮች ትሰጣለች። ከተማዋ ሁል ጊዜ በሽግግር እና በልማት ላይ ትሳተፋለች፣ እንዲሁም ለኦር ይሁዳ እና ለኦኖ ሸለቆ ነዋሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው ኑሮ ለመስጠት በዕለት ተዕለት ጉዳዮች ሁሉ ውስጥ ለማሻሻል ትጥራለች።

በነባር እና በአዳዲስ ነዋሪዎች ላይ ያለው ትልቅ ኢንቨስትመንት፣ ኦር ይሁዳን የኦኖ ሸለቆ እንቁ ለማድረግ የታቀደውን የከተማዋን ዋና ግብ ያመላክታል፣ ከተማዋ በሁሉም መስኮች የላቀ ደረጃ ለመድረስ እንዲሁም ለነዋሪዎቿ በርካታ ጥቅሞችን እና ጥራት ያለው ኑሮን ለማበርከት ትጥራለች።

መርሃግብሮች እና ፕሮጀክቶች

ኦር ይሁዳ እንደ ትምህርት፣ የከተማ ውበት፣ ባህል፣ መሰረተ ልማት እና ልማት፣ የኑሮ ጥራት፣ ስፖርቶች፣ የሃይማኖት አገልግሎቶች እና ሌሎች ባሉ መስኮች የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ እና መሪ ለመሆን የምታልም የበለፀገች ከተማ ናት።

በ2016፣ በከተማው 'ዮቬሊም' ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የትምህርት ማሻሻያ የተጀመረ ሲሆን ከረጅም ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ርዕሰ መምህር የስድስት ዓመታት የትምህርት ማዕቀፍ እንዲመራ ተመርጧል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የነበረው በሁለተኛ እና ከፍተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የነበረው ክፍፍል ተዘርዞ ልዩ ትኩረት ለትምህርት ስኬታማነት ላይ የተሰጠ ሲሆን ለከፍተኛ ተማሪዎች የፔዳጎጂ ፕሮግራሞች ምርጫ ተስፋፍቷል። እነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች ለኦር ይሁዳ ተማሪዎች ስኬቶች እና ከፍተኛ ደረጃዎች ያበረክታሉ እንዲሁም ኩራት ይጨምራሉ። ከተማው በትምህርታዊ ስኬት፣ በብቃት እና በስኬት፣ ሌሎችን በመርዳት እና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ በማተኮር እና በመፍታት በከተማዋ ሁሉ ባሉ ሌሎች ትምህርት ቤቶች እና መዋእለ-ህፃናት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። እነዚህ ተግባራት የከተማዋን ነዋሪዎች አንድ ለማድረግ አስተዋፅ ያደርጋሉ።

የሚያምር መልክን በመስጠት የከተማ ነዋሪዎችን እና ጎብኝዎችን ለማስደሰት የኦር ይሁዳ ማዘጋጃ ቤት የከተማዋን የህዝብ ስፍራዎች፣ አደባባዮች እና ጎዳናዎችን መምረጥን እና ማሻሻልን ያከናውናል።

ባህልን በተመለከተ ደግሞ ኦር ይሁዳ ለሁሉም ዘርፎች እና ታዳሚዎች የተለያዩ ዝግጅቶችን ታስተናግዳለች። ነዋሪዎቹ በከተማዋ መሃል በሚገኘው እና 450 ሰዎችን የመያዝ አቅም ባለው አስደናቂ የባህል አዳራሽ ይጠቀማሉ። ተጨማሪ ዝግጅቶች በከተማው የትያትር ማሳያ ማዕከል በሆነውና የኦር ይሁዳ እና በአከባቢው ያሉ ተማሪዎች ሙዚቃና ዳንስ በማጥናት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬት በሚበቁበት “የሙዚቃ እና ዳንስ ማእከል” ውስጥ ይስተናገዳሉ።

በ2017፣ ኦር ይሁዳ በከተማዋ በሰሜን እና በምዕራብ በኩል የ5,020 ቤቶች ግንባታን የሚፈቅደውን እና የከተማዋን የወደፊት ገጽታ የሚቀይረውን ዋና የከተማ ልማት ስምምነት ተፈራረመች። በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የገንዘብ ሚኒስትር - ሚስተር ሞሼ ካህሎን እና በቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር - ሚስተር ዮአቭ ጋላንት በተፈረመው ስምምነት መሰረት የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት ለማሻሻል በተለያዩ የከተማዋ ነባር እና አዳዲስ ሰፈሮች ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት እንዲደረግ መንግስት በግምት ወደ 1.5 ቢሊዮን ሼቅል ለማስተላለፍ ቃል ገብቷል።

የከተማው አርማ

የኦር ይሁዳ አዲስ የከተማ አርማ በ2017 የተመረቀ ሲሆን ከተማዋ የጀመረችውን አዲሱን አቅጣጫ ያንፀባርቃል። አርማው የተሠራው ከመኻል ላይ ከአንድ ቦታ ተነስተው ወደተለያዩ አቅጣጫዎች በሚሄዱ የጂኦሜትሪክ ቅርጾች ነው። የቅርጾቹ ጥምረት “የከተማው ስም አካል የሆነውን “OR” [ብርሃን] የሚለውን ቃል ይፈጥራል። በስተቀኝ በኩል ያለው የጂኦሜትሪክ ቅርፅ (በብርቱካናማ) የእንግሊዝኛ ፊደል Cን ይፈጥራል፣ ይህም ሴንተር የሚለው ቃል የመጀመሪያ ፊደል ነው።

የከተማዋ የተመረጠው መፈክር “መርካዝ ሼል ሀ-መርካዝ” [“የማዕከከል”] ሲሆን ይህም በኦኖ ሸለቆ መኻል ላይ፣ በዳን ክልል መኻል ውስጥ እና በሃገረ እስራኤል መኻል ላይ በመሆን ከተማዋ ያላትን ስትራቴጂክ አቀማመጥ ያሳያል።

በቀኝ በኩል ያለው ብርቱካናማ ክብ የዝግጅቶች መዕከልን፣ የነዋሪዎቹን መልካምነት እና በኦር ይሁዳ ውስጥ የሚገኙትን ባህሎች ስብጥር መልካምነት ያመለክታል። በግራ በኩል ያለው አረንጓዴ ቀስት በየትኛውም አቅጣጫ ወደ የትኛውም ቦታ የሚወስድውን መንገድ እንዲሁም በዳን ክልል አረንጓዴ ማዕከል ውስጥ ያለውን የአኗኗር ዘይቤ ያመለክታል። ሰማያዊው ቀጥ ያለ ዘንግ ከተማዋ የምትሄድበትን አቅጣጫ የሚያመላክት ነው - ወደ ሰማይ እና ከዚያም አልፎ “የሚገድበን ሰማይ ነው” የሚለውን ያመለክታል።

ከኦር ይሁዳ አዲሱ እና ዘመናዊው አርማ ጎን ለጎን በ1998 በግራፊክ ዲዛይነር ላቪ ፍሬንች ዲዛይን የተደረገው የከተማዋ አሮጌ አርማ ተጠብቆ ቆይቷል። በአሮጌው የከተማው አርማ ላይ፣ ፀሐይዋ የከተማዋን ብርሃን እና ስሟን ትወክላለች። በተጨማሪም አርማው ረጃጂም ሕንፃዎችን እና ኦር ይሁዳን የሚገልጹ ነጠላ ቤቶችን ያሳያል። በተጨማሪም፣ ተሽከርካሪ ጎማ እና የልብ ምት መስመር ዝቅተኛ ቴክኖሎጂ እና ከፍተኛ የቴክኖሎጂ የሆኑ የከተማ ኢንዱስትሪን የሚያመለክታል። የአሮጌው አርማ የታችኛው ክፍል ዛፎችንና አረንጓዴ ቦታዎችን ያሳያል።