ርዕደ መሬት የሚከሰተው ምንም አይነት የማስጠንቀቂያ ምልክት ሳይሰጥ ነው። በርዕደ መሬት መከሰት ወቅት የሚከተሉት እንዲሚያጋጥሙ እንጠብቃለን:

  • የመሬት ወይም ወለል እንቅስቃሴ፤
  • የተሰቀሉ ቁሶች በአብዛኛው ይነቃለቃሉ/ ይወዛወዛሉ (ምሳ፡ ተክሎች)፤
  • መጠነኛ የመደበት ስሜት ይፈጠርብዎታል፤
  • እንስሳት የመቅበጥበጥ ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ - ሊናደፉ፣ ሊቧጥጡ ወይም ሊዋጉ ይችላሉ።

በርግጥ የርዕደ መሬት ክስተት በራሱ በሰው ልጅ ህይወት ላይ ጉዳት አያደርስም።

የእዕደ መሬት መከሰትን ተከትለው የሚፈጠሩ እጅግ የተለመዱ የጉዳት ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:

  • ህንጻዎች ወይም የህንጻ አካሎች መናድ፣
  • (በተለይም በትላልቅ ህንጻዎች ላይ) የመስኮት መስታወቶች እና መስታወቶች መሰባበር፤
  • በጋዝ መፍሰስ ወይም የኤሌክትሪክ መስመሮች መገናኘት ምክንያት የሚነሳ እሳት/ቃጠሎ፣
  • በሚወድቁ የኤሌክትሪክ መስመሮች የተነሳ የሚፈጠር የሞት አደጋ
  • ፍርሀትና ጭንቀት የሚፈጥረው የልብ ድካም

 

ቤተሰብን ማዘጋጀት

መኖሪያ ቤትን ማዘጋጀት

ማዕድ ቤትን ማዘጋጀት

የአደገኛ ቁሶች አቀማመጥ

መኝታ ክፍል

ባኞ ቤት

መኖሪያ ክፍል፣ የምግብ ክፍልና የስራ ክፍል

መጋዘንና የሰርቪስ ቦታዎች

ለርዕደ መሬት ቤተሰብን ማዘጋጀት

  • በርዕደ መሬት ጊዜ መከተል የሚገቡ ባህሪያትን መለማመድ; ከትላልቅ/ከባድ የቤት እቃዎች ስር ገብቶ መደበቅና የእቃዎቹን አንዱን እግር አጥብቆ መያዝ- መደበቅ፣ መሸፈንና አጥብቆ መያዝ።
  • ርዕደ መሬቱ ካበቃ በኋላ ቤተሰቡ መልሶ የሚገናኝበት የመሰባሰቢያ ቦታ ማዘጋጀት። የመሰብሰቢያ ቦታ ለመኖሪያ ቤት በቅርበት የሚገኝ ወይም ሁሉም የቤተሰቡ አባላት በቀላሉ ማግኘት የሚችሉት ለምሳሌ እንደ የህዝብ ፓርክ ያለ ቦታ መሆን አለበት።
  • ከልጆችዎ ጋር ርዕደ መሬት ሊከሰት ስለሚችልበት እድል ይወያዩ እንዲሁም ክስተቱ በትምህርት ቤት ወይም መኖሪያ ቤት ውስጥ እያሉ ቢያጋጥም ምን ማድረግ እንዳለባቸው በመንገር ያለማምዷቸው።
  • በመኖሪያ ቤትዎ ውስጥ እጅግ አመቺ ቦታ ይምረጡ እና ሁሉንም የቤተሰቡን አባላት እዚህ ቦታ እንዲጠለሉ መመሪያ ይስጧቸው።
  • ከትላልቅ የቤት እቃዎች፣ ትላልቅ መስኮቶች፣ ስዕሎች፣ ወዘተ ይራቁ።
  • ዋና የጋዝ ባልቦላና የውሀ መክፈቻዎች እንዲሁም ዋና የኤሌክትሪክ ማብሪያ ማጥፊያ የት እንደሚገኙ ለይተው ይወቁ። ጋዝ የሚፈስበት ሁኔታ ከተፈጠረ ዋናው የጋዝ ባልቦላ መዘጋት አለበት።
  • ለድንገተኛ ሁኔታዎች አስፈላጊ ተብለው የተገለጹ እቃዎችን የያዘ የድንገተኛ ጊዜ እቃ መያዣ አስቀድመው ያዘጋጁ፡ በባትሪ የሚሰራ ፍላሽላይትና ራዲዮ (ተቀያሪ ባትሪዎችን ጨምሮ)፤ የአንቲባዮቲክ ክሬም፣ ህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች፣ መመረዝን ማርከሻ፣ የውሀ ማከሚያ መአድኖች፣ ፋሻ፣ ማሸጊያ፣ ቁስል ማሰሪያ፣ መጠገኛ፣ የትኛውንም ቤተሰቡ በቋሚነት የሚወስዳቸው መድሀኒቶች፣ የአይን መነጽር የሚይዝ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ እቃዎች የሚይዝ የእቃ መያዣ፣ የህክምና ሰነዶች፣ ተቀያሪ ልብስ፣ የመታወቂያ ሰነዶች፣ ገንዘብ፣ ክብሪቶች፣ ሻማዎች፣ ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውል ቢላዋ እና የግል ንጽህና መጠበቂያ እቃዎች፣ ልዩ የህጻናት እቃዎች።

እቃዎቹ በቤት ውስጥ ደህንነቱ በተጠበቀና ማግኘት የሚቻልበት ቦታ መቀመጥ አለባቸው። ሁሉም የቤተሰቡ አባላት እቃዎቹ የት እንደሚገኙና እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው። ከእነዚህ ሁሉም ዝግጅቶች በተጨማሪ በገንዘብ ረገድ ዝግጁ መሆን እና የርዕደ መሬት ጉዳት የመድን ዋስትና ሽፋን መግዛት እጅግ ጠቃሚ ነው።

መኖሪያ ቤትን ለርዕደ መሬት ማዘጋጀት

የሚደርስ ጉዳትን ለመቀነስ መኖሪያ ቤትን ማዘጋጀት

መኖሪያ ቤት ከመገዛቱ በፊት ቤቱ ርዕደ መሬት የመቋቋም አቅም ያለው መሆኑ መረጋገጥ አለበት። በተቻለ መጠን ተደጋጋሚ የውስጥ መናወጥ በሚያጋጥምበት ቦታ፣ ወይም ለመሬት መንሸራተት ወይም ፍሰት የሚያጋልጥ ምቹ ያልሆነ ቦታ ወይም የሚያንሸራት ጉብታ ቦታ ላይ የሚገኝ ቤት መገዛት የለበትም። በእያንዳንዱ እነዚህ ሁኔታዎች ማንም ሰው መዋቅሩ ርዕደ መሬትን የሚቋቋም መሆኑን ለማረጋገጥ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ይህ የሙያ ማረጋገጫ የተሰጣቸው ሙያተኞችን ማማከርን የሚጠይቅ ሲሆን መዋቅሩን የሚመረምርና እንደ አስፈላጊነቱ የማጠናከሪያ ምክረ ሀሳቦችን የሚሰጥ መሀንዲስ ይዞ መገኘት ጠቃሚ ነው።

ማዕድ ቤትን ለርዕደ መሬት ማዘጋጀት

የርዕደ መሬት አደጋ በሚከሰትበት ወቅት የቤተሰብ አባላት ተሰብሮ በሚወድቅ መስታወት፣ የሚረጩ አደገኛ የጽዳት ፈሳሾች ወይም የሚወድቁ ቁሶች ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል። እነዚህን ለመከላከል የሚከተሉት እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው:

  • በማድ ቤት በሮች፣ ቁምሳጥኖችና መሳቢያዎች/ መደርደሪያዎች ላይ ርዕደ መሬት በሚያጋጥምበት ወቅት እንደተዘጉ እንዲቆዩ ቁልፍ ወይም መወርወሪያ መግጠም (ተጨማሪ ማግኔቶች በቂ አይደሉም)
  • ትላልቅ ድስቶች/መጥበሻዎች/ሳህኖችን ከመደርደሪያ የስረኛው ክፍል ያስቀምጡ
  • በመደርደሪያ ውስጥ የተደረደሩ እቃዎች እንዳይወድቁ ለመከላከል ማቆሚያ ይግጠሙ። የሚሰበሩ እቃዎች በሲልከን ወይም የሚያጣብቁ መያዣዎች ውስጥ መቀመጥ አለባቸው።
  • የሚሰበሩ ሳህኖች በሳጥን ታሽገው ከእቃ መደርደሪያ የስረኛው ክፍል መቀመጥ አለባቸው።
  • ለመብራት አቃፊዎች፣ ሰአቶች፣ መስቀያዎችና ሌሎች የኩሽና እቃዎች መስቀያዎች ማጠናከሪያ ያድርጉላቸው።
  • ተዟዟሪ የጋዝ ቱቦ ይግጠሙ.
  • በጎማ የሚንቀሳቀሱ ከባድ እቃዎች ወለል ላይ መታሰር አለባቸው።

የአደገኛ እቃዎች አቀማመጥ

  • ሁልጊዜም በመደበኛነት ጥቅም ላይ የሚውሉ እቃዎች ብቻ ቤት ውስጥ መቀመጥ አለባቸው
  • ክሎሪንና ሌሎች ማንጫዎችን ለያይተው ያስቀምጡ – እነዚህ ሁለቱ ከተቀላቀሉ መራዥ ጋዞችን ይፈጥራሉ።
  • ጸረ ተባይ፣ ነጭ ጋዝ፣ የቀለም መቀላቀያ እና የመሳሰሉት በግርግዳ ላይ የሚገጠም በአግባቡ በሚዘጋ የቁም ሳጥን መደርደሪያ ውስጥ መቀመጥ አለባቸው
  • ጠርሙሶች ወይም ጆጎች ለሚቀመጡባቸው ክፍት መደርደሪያዎች እቃዎቹ ወለል ላይ እንዳይወድቁ ለመከላከል ልዩ የመክፈቻ ኬብል ይግጠሙ።
  • ገንቦና የእቃ መያዣዎችን ከድነው በአግባቡ ይዝጉ።
  • ነጭ ጋዝን እንዳይተን ለመከላከል በልዩ መያዣዎች ይያዙ።

መኝታ ክፍል

መኝታ ክፍልን ማዘጋጀት ማለት ሰዎችን በሚወድቁ እቃዎች እንዳይጎዱ መከላከል፣ ክፍት የማምለጫ መስመር እንዲያገኙ ማስቻል እና ወሳኝ እቃዎችን (ፍላሽላይት፣ የአይን መነጽር፣ ጫማ፣ ልብስ፣ አስፈላጊ መድሀኒቶች፣ ራዲዮ፣ ትራንዚስተር) እንዲያገኙ ማስቻል ማለት ነው።

  • እንደ የምሽት መደገፊያዎች፣ ድሬሰሮችና የመጽሀፍ መደርደሪያዎች ያሉ የቤት እቃዎችን ግርግዳ ላይ ያጠናክሩ። ይህ የእቃዎቹን የጀርባ ክፍል በመብሳት እና ግድግዳ ላይ በማሰር ሊደረግ ይችላል (እቃዎቹ ጠብቀው መያዛቸውን ያረጋግጡ)። ማሰሪው በቂ ካልሆነ ተጨማሪ ብረት በመጠቀም ግድግዳ ላይ ሊታሰሩ ይችላሉ።
  • ብዙ የመጽሀፍ መደርደሪያዎች ጎን ለጎን የሚገኙ ከሆነ የበለጠ ፀንተው እንዲቆሙ ለማስቻል መደርደሪያዎቹ እርስ በርሳቸውና ከግድግዳ ጋር መታሰር አለባቸው።
  • ስእሎች ወይም መስታወቶች ሰው ላይ ሊወድቁ ስለሚችሉ እነዚህን ከአልጋ ወይም ወንበሮች በላይ አይስቀሉ።
  • በተቻለ መጠን የመጽሀፍ መደርደሪያዎችና ድሬሰሮችን ክፍት የመውጫ ቦታ ለመፍጠር መውጫ ቦታ ላይ አያስቀምጡ
  • ከባድ እቃዎችን ከመደርደሪያ በታች ያስቀምጡ
  • ቁም ሳጥኖችና መደርደሪያዎችን በቁልፍና መወርወሪያ ይቆልፉ።

ባኞ ቤት

በባኞ ቤት ውስጥ በጣም ከባድ ጉዳት የሚያጋጥመው በተሰበሩ መስታወቶች - መስታወቶች.፣ ጠርሙሶችና መድሀኒቶች መውደቅ፣ መሰበርና መጋረድ ምክንያት ነው። ምንም እንኳን በጣም ብዙ አይነት ምርቶች በፕላስቲክ ጠርሙሶች ታሽገው ለገበያ እየቀረቡ ቢሆንም እንደ ሽቶዎች ያሉ አንዳንድ እቃዎች በሚሰበሩ ጠርሙሶች ይታሸጋሉ።

  • በማይሰበሩ መያዣዎች የታሸጉ ምርቶችን መግዛት ይመከራል
  • የሚሰበሩ የእቃ መያዣዎችን በባኞ ቤት ወይም መታጠቢያ ቤት አይተዉ
  • የመድሀኒት መደር በጥሩ ቁልፍ ይቆልፉ – በተለይም ለህጻናት ደህንነት
  • እንደ ፎጣ ያሉ ቀላል እቃዎችን ብቻ በክፍት መደርደሪያዎች ውስጥ ያስቀምጡ
  • የጽዳት እቃዎችን መወርወሪያ ወይም ቁልፍ ባለው ጉርድ መደርደሪያ ውስጥ ያስቀምጡ።

ሳሎን፣ የምግብ ክፍልና የመስሪያ ክፍል

  • ኮምፒውተሮችን፣ የድምጽ ሲስተሞችን፣ ቲቪዎችን፣ የቪዲዮ ማጫወቻዎችን፣ ወዘተ ከማስቀመጫቸው ጋር ማሰር። እነዚህ በኬብል ወይም ገመድ ሊታሰሩ ይችላሉ። ማሽኖቹ ጠረጴዛ ወይም ግድግዳ ላይ መታሰር አለባቸው።
  • መስታወቶችና ስዕሎችን ከሚስማር ይልቅ በመንጠቆ መስቀል። ለትላልቅ ስእሎች ወይም መስታወቶች ሁለት መጠቀም ይመከራል።
  • መስታወቶች ወይም ስዕሎችን ሰው ላይ ሊወድቁ በሚችሉበት ቦታ ለምሳሌ ከአልጋ ወይም ወንበር በላይ አይስቀሉ።

መጋዘንና የሰርቪስ ቦታዎች

  • የውሀ ማሞቂያን ወለል ወይም ግድግዳ ላይ በሽቦ ማሰር ይመከራል።
  • ወደ ውሀ ማሞቂያው የሚያስተላልፉ የውሀና ጋዝ ቱቦዎች ተነቃቃይ መሆን አለባቸው
  • መራዥ ወይም ተቀጣጣይ ነገሮች አደጋ በሚቋቋሙ ምልክት የተደረገባቸው መያዣዎች ውስጥ መቀመጥ አለባቸው። መደርደሪያዎቹ ጠንካራ ቁልፍ ባለው ጉርድ መደርደሪያ ውስጥ መቀመጥ አለባቸው። እነዚህ አየር በጥሩ ሁኔታ ማግኘት በሚችል ቦታ ቢቀመጡ ይመከራል።
  • የእሳት ማንደጃ ወይም የማገዶ እንጨት ማቀጣጠያ ምድጃዎች ወለል ላይ ጠብቀው መታሰር አለባቸው
  • በቤት ውስጥ የእሳት ማጥፊያ ማስቀመጥ ይመከራል።